ከ፫ቱ አካላት ፩ዱ አካል ወልድ ቅድመ ዓለም ከአብ አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባሕርይ ተወልዶ ፶፻፭፻ (5500) ዘመን ሲፈጸም ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ ሰው ሁኖ ተወለደ፡፡ መለኮት ከሥጋ ሥጋ ከመለኮት እንበለ ውላጤ፣ እንበለ ቱሳሔ፣ እንበለ ቡአዴ፣ እንበለ ምንታዌ ፩ አካል ፩ ባሕርይ ሆነ " ፩ ውእቱ እምቅድመ ይሠጎ ወ፩ ውእቱ እምድኅረ ተሠገወ " ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ሰውም ከሆነ በኋላ ባሕርዩ ፩ ነው " አንዳለ ቄርሎስ፡፡ ጎርጎርዮስም " ውእቱ እግዚአብሔር ዘኮነ ሰብአ ወውእቱ ሰብእ ዘኮነ አምላክ በተዋህዶተ መለኮት " "በተዋህዶ ሰው የሆነ አምላክ አምላክም የሆነ ሰው እሱ ብቻ ነው" ብሏል፡፡ ሥጋም በተዋህዶተ ቃል እንደከበረ ምስክር ዮሐንስ አፈወርቅ " ወኢረሰየ ሎቱ ህፀተ ሶበ ኮነ ልብሰ አባሎ ወዳዕሙ ሥጋ ረብሀ ስብሐተ ሶበ ኮነ ልብሶ ለፈጣረ" ብሏል "በሥጋ የነበረ ንዴት በተዋህዶተ ቃል ጠፋ የቃል ክብር ለሥጋ በተዋህዶ ገንዘቡ ሆነ" ብሏል፡፡
ተዋህዶ ሃማኖት ሳይማሩ በድፍረት ልመርምርህ ሲሉት የማይመረመር የተሠወረ ነው፡፡ ወጥቶ ወርዶ ተምሮ በፍቅር በትህትና በግብረ ገብነት ሁኖ ሲመረምሩት ግን እንደ ፀሐይ የበራ ነው፡፡ የሃይማትን ትምህርት መማር አዋቂ ነኝ ለማለት፣ ራስን ለማግነን፣ ሰውን ለመንቀፍ፣ ውሳጣዊ ዕውቀት ሳይኖር በዝምተኝነት አዋቂ መስሎ በመታየት አይደለም፡፡ በሥጋየ ምን ፈተና ይገጥመኝ ይሆን ? በነፍሴስ ምን ዕንቅፋት ይቆየኝ ይሆን እያሉ በማዘን በመጸለይ ስለኛ ቤዛ ሆኖ የሞተልን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕማሙን ሞቱን ለማስታወስና እሱን ለመከተል ነው እንጂ፡፡

ከ፫ቱ አካላት ፩ዱ አካል ወልድ እኛን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ለማዳን ስለኛ ሰውም ሆኖ በሥጋ ተወለደ ባልን ጊዜ ፪ት ልደት እንዳለ እናምናለን፡፡ መጀመሪያ ዓለም ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው ፪ኛም ፭ሺህ ከ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ከድንግል ማርያም የተወለደው ልደት ነው፡፡ ከተወለደም በኋላ ከኃጢአት በቀር ሰው የሚሠራውን ሥራ ሁሉ እየሠራ አደገ ፡፡ በዚህ ዓለም "፫ ዓመት ከ፫ ወር አስተምሮ ስለእኛ የሞት ፍርድን ተቀብሎ በመስቀል ተስቅሎ ሞተ፡፡ በሞቱም ዓለምን አድኖ ፫ መዓልት ፫ ሌሊት በከርሠ መቃብር አድሮ ተነሣ፡፡ ከተነሣም በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ እየታየ ጉባኤ ሠርቶም መጽሐፈ ኪዳንን እያስተማረ በምድር ላይ ፵ ቀን ከቆየ በኋላ በመላእክት ምስጋና በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱ ቀኝ (ዕሪና) ተቀመጠ መላእክት ተገዙለት ፩ኛ ጴጥ ፫፡፳፪፡፡ ዳግመኛ መጥቶ ሰማይና ምድርን ያሳልፋል ለጻድቃን ይፈርዳላቸዋል በኃጥአንም ይፈርድባቸዋል ማቴ ፳፭፡፴፩፡፡ ክርስቶስ ቃለ አብ ወመንፈስ ቅዱስ፣ ድንግል ማርያምንም በአማን ወላዲተ አምላክ ወላዲተ ቃል ብሎ ማመን ነው ፡፡ እንዲህ ካልሆነ ተዋህዶ ማለት አይገኝም ፡፡ እርሱም ባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደሰማይ የወጣ የለም ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር እርሱም በሰማይ የሚኖር ነው፡፡ ዮሐ ፫ ፡፲፫ በማለቱ ፩ አካል ፩ ባህርይ መሆኑን አስረድቶናል፡፡
ይቆየን!
No comments:
Post a Comment